''ነግበኔ'' የምትባል አባባል አለች።


 ''ነግበኔ'' የምትባል አባባል አለች።

ይነበብ 👉አንድ ወዳጀ ያደረኝ አሳዛኝ አጋጣሚ ነው።
በእለተ እሁድ መስከረም 22 ቀን 2015 ዓ.ም ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አልጋ ይዞ የተኛ ቤተሠብ ለመጠየቅ አቀናሁ። እንደ ወጉ የሚጠጣና የሚበላ ምግብ ይዤ በፋና በኩል ባለው በር ከጠዋቱ 4:20 አካባቢ ደረስኩ። ከበሩ አካባቢ ብዙ ሰው ቆሟል እኔም ጠጋ ብዬ ታካሚ ለመጠየቅ መጥቼ ነበር መግባት እችላለሁ ስል አንዱን ከፊት ለፊት ያገኘሁትን ጥበቃ ጠየኩ፣ አይቻልም 11:00 ነው መግባት የሚቻለው ሲል በስጨት ብሎ መለሰልኝ። እኔም ከውስጥ ካለ አስተማሚ ዘንድ ስልክ ደውዬ በር ላይ አላስገባም አሉኝ ና እስኪ አልኩት።
የእርሱን መምጣት እየተጠባበኩ አስገቡን አናስገባም የሚሉ ንትርኮችን መመልከትና መታዘቤን ቀጠልኩ። ነገርግን አንድ ከወጣትነት ከፍ ያለች ሴት በነጭ ፌስታል መድኃኒት ነገር ይዛ ከጥበቃዎች ጋር ጮክ ብላ <>እባካችሁ ለእናቴ መድኃኒት እንድገዛላት ዶክተሩ አዝዞኝ ነው እባካችሁ አስገቡኝ እባካችሁ>> እያለች ትለምናቸው ጀመር። እነርሱም አትችይም መግቢያ ወረቀት የለሽም የሚል ምላሽ ይሰጧታል። እሷም ደጋግማ መለመኗን አላቆመችም <<ይህንን መድኃኒት ካልወሰድኩ እናቴ ትሞትብኛለች፣ እናቴ ጋር ከዶክተሩ ውጭ ሌላ አስተማሚ የለም እባካችሁ>> እያለች ለመነች የሚሰማት ግን አልነበረም።
በዚህ መሃል ስጠብቀው የነበረው አስታማሚ ግለሰብ መጣና የያዝኩትን እህል ውሃ ከመግቢያው በር አካባቢ ሰጠሁት እና እስኪ እንድገባ ጥበቃዎችን ጠይቅልኝ ብዬው ወደ መግቢያው በር ተጠግተን የእርሱን በብጣሽ ወረቀት የተጻፈች የሕክምና ORC (የቀዶ ጥገና ፕሮግራም ወረቀት) አሳያቸውና ታማሚ ሊጠይቅ ስለሆነ አብሮኝ ይግባ ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም ወረቀቱን አዩና አንተም አትገባም ብለውት አረፉ። ለምን ሲል ጠየቀ? በዚህ ወረቀት መግባት አይቻልም አሉት፤ እሱም እንዴ እኔ እኮ በዚህ ነው ስወጣ ስገባ የሰነበትኩት አሁንም በዚህ በር እኮ ነው የወጣሁ አላቸው። ስትወጣ ተናግረህ መውጣት ነበረብህ ዞር በል ብለው የተወጠረች ገመድ አለችና ከዚያ ውጭ ሁን ብለው ገፈተሩት።
እኔም ወረቀት ያልያዘችው እና መድኃኒት ልገዛ ነው እያለች ሳታቋራጥ የምትለምነዋን እንስት ወረቀት የለሽም አላስገባም ሲሉ የነበሩት የታካሚ ወረቀትን ይዞ አላስገባም ሲሉ የበለጠ ትዝብቴና ትኩረቴ እየሆነ ያለውን የብዙ ሰዎች ልመና አንዳንዱ ተናዶ ሲመለስ መመልከቴንና መታዘቤን ቀጠልኩ። ደቂቃዎች ነጎዱ ሰዓታት አለፉ። በመሃል አንድ መልዕክት ከሆስፒታሉ ውስጥ ወደ በር መጣ። እሱንም ያወኩት የጩኸት ድምፅ ስሰማ ነው። ለካስ ያቺ መድኃኒት ገዝታ እናቷን ለማዳን ከበር ደርሳ በጥበቃዎች አትገቢም በሚል ምክንያት እናቷ እንዳረፈች መርዶ ደርሷት ነው።
በዚህም ወቅት ጥበቃዎች ተደናገጡ በር ላይ ለታማሚ ምግብ፣ መድኃኒት ይዞ ሲጠባበቅ የነበር እና ለመጠየቅ ቆሞ የነበረ በሙሉ ግቡ አሉ ገባን። በኋላ ቆም ብዬ ግን ለምን ሁላችንን አስገቡን ብዬ ራሴን ስጠብቅ የሆነ ነገር መጣልኝ እሱም ምንአልባት በጥብቃዎች አላስገባም ምክንያት እናቴ ሞተች ብላ ብታመለክት በር ላይ ይሄን ትእይንት ስንመለከት የነበርን እማኝ እንዳንሆን ፈርተው እና ራሳቸውን ከተጠያቂነት ለማውጣት ይሆን ብዬ ገመትኩ። ብቻ በር አካባቢ የነበረው እንግልት አሰልቺ ነበር።
ለማንኛውም በር አካባቢ ላሉ ጥበቃዎች ተገቢውን ስልጠና መስጠት ቢቻል መልካም ነው።
ወደ ሆስፒታሉ ለሚመጡ ታካሚዎችም ሆነ አስታማሚዎች ከበር ጀምሮ እንዴት መቀበልና ማስተናገድ እንዳለባቸው ግንዛቤ መፍጠር ቢቻል።
ምክንያቱም ሕክምና ቦታ የሚመጣ ሰው ለመዝናናት እንደማይመጣ ይታወቃል፣ አስታማሚዎችም ቢሆኑ በመሃል በድንገት ምን እንደሚፈጠር ስለማያውቁ በድንጋጤ የበር ላይ መግቢያና መውጫ ካርድ ሳይዙ ረስተው ሊወጡ ስለሚችሉ ሌላ አማራጭ መግባት የሚችሉበት ነገር ቢኖር መልካም ነው። ሕግና ሥርዓትን ጠብቆ ማስተናገድ ተገቢ ነው። አንዳንዴ ግን Tolerate ማድረግ የሚገባቸውን ነገሮችን በተገቢው መልኩ በቀናነት መመልከትና ማስተናገድ ይገባል።
በዚህም ወቅት አንድ ጥበቃ የሚገርም የሚያሳቀቅ ምላሽ ሲሰጥ ነበር፣ ታማሚ ልጠይቅ ነው ይለዋል ለምን ታማሚው አይመጣም አትገባም ሲል ሰምቼ ተገርሜያለሁ። ኧረ ደግሞ አንዱ የመግቢያ ካርዱን አሳይቶ ሊገባ ሲል ቆይ ቆይ ወዴት ነው ይሔ ያንተ ካርድ አይደለም አትገባም አለው፣ ሰውዬውም ቀበል አድርጎ እንዴ ለምን ካርዱ ላይ የተጻፈውን እና ይሔው መታወቂያዬን አስተያየው ይልና መታወቂያውን ይሰጠዋል።
ጥበቃውም አትችልም አልኩህ አትገባም ስምህ ምን ያደርግልኛል ይለዋል። በዚህ ነገር ምን ታዘብኩ ይሔ ጥበቃ ማንበብ መጻፍ እንደማይችል ወይንም የሆነ ነገር ፈልጓል ብዬ እንድጠረጥር አድርጎኛል።
ብቻ ዛሬ የነበረኝ ትዝብት ይሔው ነውና ትዝብቴን በመልካም ጎን ወስዳችሁ የሚመለከታችሁ አካላት ለመፍትሔው ብትሰሩበት መልካም ነው እላለሁ።
መስከረም 22 ቀን 2015 ዓ.ም
ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ፥ አዲስ አበባ ተፃፈ።

Comments

Popular posts from this blog

New Jobs At Abay Bank(For Fresh Graduate) 👁 Position: Customer Service Officers (CSO) – II ✅ Experience:- 0 year/Fresh Graduates ✅ Qualification: BA degree in Management or Economics or Accounting & Finance or Marketing or Banking & Finance, Business Administration and any business related field of study. 📌Deadline October: 14- 2022 📌ሰለ ሰራው ሙሉ መረጃ ለማየት ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ👇👇 👉Read Detail:- https://bit.ly/3SNQMWN 🔰ከተለያዩ ድርጅት የሥራ ማስታወቂያዎች በዚህ ሊንክ ዌብሳይቱ ላይ ይመልከቱት👇👇 =>See Detail:- https://ethioworks.com 🍎Telegram:- https://t.me/BeeksisaaHojii Don't forget to Share 👥 Thank you!